ተላልፎ የተሰጠብንን የአባቶቻችን ርስት ቀይባህርን የማስመለስ ግዴታ አለብን ‼️
አዲሱ ትውልድ ቀይ ባህርን የማስመለስ ግዴታ አለበት። ቀይ ባህር ርስታችን ነው። ቀይ ባህር ያለምክንያት ያጣን ሃብታችን ነው። አሁን ግን በምክንያት ማስመለስ የምንችል ሃብታችን ነው። ያለምክንያት አጣን የእኛ ሃብት ስለሆነ በምክንያት እናስመልሳለን። ይህ ለዚህ ትውልድ አደራ ነው።
ቅንነት ያለው በሰጥቶ መቀበል ሊሰጠን ይገባል። አለበለዚያ እውነት ይዳኘናል። ኢትዮጵያ ደግሞ እውነት አላት። የተዳፈነው እውነት ይገለጥ፣ አለምም እውነታውን ተረድቶ ከኢትዮጵያ ጎን ቆሟል። ኤርትራም ጭምር ለኢትዮጵያ ቀይ ባህር እንደሚገባት ታምናለች። ለዚያም ነው እንቅፋት ለመሆን የምትሯሯጠው።
130 ሚሊየን ህዝብ ዙርያው ላይ አገልግሎት የማይሰጡ የግመል መጠጫና የዝንብ መጫወቻ የሆኑ ወደቦች እያሉ ከሌላ ለምና የምትኖርበት ምክንያት የለም። ወደብ አልባነትን ታሪክ ለማድረግ በሴራ ያጣነውን ቀይ ባህር መቀበል ግዴታችን ነው ‼️
Abiy Ahmed Ali
Kanuma ‼️